ወደ አጋዥ መተግበሪያ እንኳን ደህና መጡ!
ከመሠረታዊ ጸሎቶች: አቡነ ዘበሰማያት ጀምሮ እስከ መልክዐ ማርያም፣ መልክዐ ኢየሱስ እና ውዳሴ ማርያም ድረስ በድምፅ ደረጃ በደረጃ ለማጥናት፣ አነባበቡን ለመረዳት እና ለመሸምደድ የሚያግዝዎ መተግበሪያ።
አፑን ሲያወርዱ Chrome 'File might be harmful' የሚል መልዕክት ቢያመጣባችሁ አፑ ደህንነቱ የተረጋገጠ ስለሆነ 'Download anyway' የሚለውን ይጫኑ።
በአጋዥ አፕ (Agazh App) ውስጥ ምን ያገኛሉ?
ለጀማሪዎችም ሆነ የግእዝ ጸሎታቸውንና አነባበባቸውን ማጠናከር ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ሁሉን አቀፍ መድረክ
የግእዝን አነባበብ ስልት እንዲያውቁ
ከ በስመ አብ እና ከአቡነ ዘበሰማያት ጀምሮ እስከ መልክዐ ኢየሱስ ያሉትን ቃላት ትክክለኛ ድምጸትና ቅላጼ በመስማት የግእዝን ንባብ ስልት ይረዳሉ።
ትላልቅ ምስጋናዎችና መልኮችን ያካተተ
መልክዐ ኢየሱስ፣ መልክዐ ማርያም፣ ሰላም ለኪ እና ሌሎችም የውዳሴ ማርያም ጸሎቶች ደረጃ በደረጃ ለጥናት በሚያመች መልክ ተከፋፍለው ይገኛሉ።
የድምፅ አቀራረብና ሽምደዳ
ቃላቶች ለሽምደዳ በሚያመችና በትናንሽ ቡድን ተከፍለው ለጥናት በሚመች መንገድ ቀርበዋል።
ቀላል እና ማራኪ አጠቃቀም
በማንኛውም የእድሜ ክልል ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን እጅግ ቀላልና ዘመናዊ በሆነ ንድፍ የተሰራ ንጹሕ የተጠቃሚ በይነገጽ (UI)።
በ 3 ቀላል ደረጃዎች የግእዝ ጸሎት ማጥናት ይጀምሩ
"የግእዝ ጸሎትን ብለምድ ኖሮ" ማለት ቀረ፤ ዛሬውኑ በስልክዎ ይጀምሩ
አፑን ያውርዱ
ከላይ ያለውን ቁልፍ በመጫን agazh-v2.2.apk ፋይልን በስልክዎ ላይ በቀጥታ ይጫኑ(የወረደውን ፋይል Install ያድርጉ)።
ይመዝገቡ
ኢሜል እና የይለፍ ቃል(password) በማስገባት ይመዝገቡ፤ ኢሜልዎ ጋር በመግባት የተላከውን ሊንክ ነክተው ያረጋግጡ። በመቀጠል ወደ መተግበሪያው ተመልሰው ይግቡ።
በድምፅ ይለማመዱ
“ጥናት እንጀምር” የሚለውን ከነኩ በኋላ የተሰጠዎት ደቂቃ እስኪያልቅ ድረስ የሚሰሙትን ድምጽ እየተከተሉ ያጥኑ፣ ይሸምድዱ።
ስለ ሀገረማርያም ግሩፕስ (Hageremariam Groups)
እኛ ሀገረማርያም ግሩፕስ የተሰኘን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ወጣቶች ስንሆን፡ አብነት ትምህርትን የመማር እድል ሳያገኙ ኑረው በእድሜ ወደ አዋቂነት የመጡ ምዕመናን ቢያንስ መሠረታዊ የግእዝ ጸሎቶችን ማለትም አቡነ ዘበሰማያት፣ ሰላም ለኪ፣ ውዳሴ ማርያም ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን ማወቅ የሚችሉበትን መድረክ ብንፈጥር ብዙ ሰው ከእምነቱና ከጸሎት ሕይወቱ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠነክር ይረዳል በሚል ተነሳሽነት፡ ከቤተክርስቲያናችን አባቶች እና ሊቃውንት ጋር በመተባበር ይህንን መተግበሪያ ለእናንተ ማቅረብ ችለናል።
በሥራ፣ በትምህርት ወይም በሕይወት ውጣ ውረድ ምክንያት የግእዝ ጸሎትን ለመማር ጊዜ ላጡ ምዕመናን ስማርት ስልካቸውን እንደ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እንዲጠቀሙበት አስተማማኝ ድልድይ እየገነባን እንገኛለን።
ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ)
ስለ አጋዥ መተግበሪያ፣ አወራረድና አጠቃቀም ማወቅ የሚፈልጓቸው ዝርዝሮች
• 1ኛ የ 1 አመት አገልግሎት በ 200 ብር
• 2ኛ የ ህይወት ዘመን አገልግሎት በ 500 ብር… ናቸው።
እነዚህ ሁሉም ሶስት የግዥ አማራጮች ባላቸው የጊዜ ገደብ እርዝመት ብቻ የሚለያዩ ሲሆን በሚያስከፍቱት የጸሎት ምእራፎች እና አገልግሎት ላይ ግን ምንም አይነት ልዩነት የላቸውም፡፡ በአጋዥ መተግበሪያ ላይ የሚደረጉ ማንኛውም የደንበኝነት ግዥዎች እና የአገልግሎት ጊዜያት በአውሮፓውያን የካላንደር ቀመር (GC) የሚሰሉ ናቸው።